.
ዋናው ገጽ > የአገልግሎት ቡድኖች > የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት

የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት

የአገልግሎቱ ራእይ

  • ሌሎችን ለክርስቶስ ለመማረክ ስንጣጣር የእኛኑ ልጆች በእግዚአብሔር መንግስት እንዳናጣቸው!
  • ለክርስቶስ የተማረከ ትውልድን ማፍራት!
  • ቤተክርሰቲያንን የሚረከብ ትውልድን ማፍራት!
  • በእኛ ትውልድ ዘንድ ያለው የእግዚአብሔርን እሳት ለሚከተለው ትውልድ ማስተላለፍ!
  • ከእኛ ይልቅ የጨከኑ የእግዚአብሔር ሰዎች እንዲወጣቸው!

የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት ዓላማ

  1. የደህንነት ውሳኔ ያላደረጉ እንዲወስኑ መርዳት
  2. የወሰኑት በእግዚአብሔር ቃል ተኮትኩተው እንዲያድጉና እንዲጠነክሩ መርዳት
  3. በትምህርት ቤትና በሕብረተሰብ ታዳጊ ወጣቶች የሚገነባባቸውን ምሽግ በእግዚአብሔር ቃል ማፍረስ
  4. የክፋትን አሰራር ማጋለጥ ማፍረስና መመከት
  5. ለቤተሰብና ለቤተክርስቲያን የበኩላችንን እገዛ ማድረግ
  6. መልካም ሕብረት በመካከላቸው እንዲፈጠር ማድረግ
  7. በትምሕርት በኑሮ ውሳኔዎች በሕይወት ጥያቄዎች ለታዳጊ ወጣቶች ድጋፍ መሆን
  8. በአምልኮና በሌላውም መድረክ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ማበርከት
  9. እግዚአብሔር ለእያንዳንዳቸው ያለውን ዓላማ እንዲያውቁ መርዳትና ማነሳሳት
  10. እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸውና ለውጥ የሚያመጡ እንዲሆኑ መርዳት

የታዳጊ ወጣቶች የመሰብሰቢያ ጊዜአት

  • ዘወትር እሁድ 10፡00 እስከ 11፡30 (በፈረንጆች ሰአት አቆጣጠር) የአምልኮና የትምህርት ጊዜ
  • በሳምንት አንዴ ወይንም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ በትንንሽ ቡድኖች በወጣቶች መሪዎች ይሰበሰባሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናሉ፣ ቁምነገር አዘል ጭውውቶችን ያደርጋሉ
  • ለወጣቶቹ እንደ እድሜአቸው የሚመጥን ትምሕርቶችን እንሰጣለን

የአገልግሎት ቡድኑ አባላት


የአገልግሎት ቡድኑ የሚሰበሰብበት መደበኛ ጊዜ፤

  • በየሳምንቱ ሰኞ ምሽት የፀሎትና እቅድ የማውጫ ጊዜ
  • በወር አንድ ጊዜ የጸሎትና የማቀጃ ጊዜ
  • በተጨማሪም እንደየአስፈላጊነቱ በስልክ ስብሰባ ያደርጋል

ንዑሳን ድረገጾች


ቋንቋ ምረጥ

ተጨማሪ ድረ ገጾች

ማስታወቂያዎች

መደበኛ (የዘወትር) ፕሮግራሞቻችን፤


  1. መጋቢዎቻችንን በሚከተለው ቁጥር ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ መጋቢ ንጉሱ ጉሌ (+46 (0)735115951) መጋቢ ወሰን ተሾመ (+46 (0)736162913)

  2. ሰኞ 10:00-14:00 የምክር አገልግሎት በወንድም ሙሴ ሃይሉ (በስልክ ቁ. 0707568264) በመደወል ልታገኙት ትችላላችሁ።
  3. ዘወትር ረቡዕ ከጥዋቱ አራት ሰዓት (10፡00) እስከ አስር ሰዓት (15፡00) የጾምና የጸሎት ጊዜ አለን
  4. ሀሙስ 18:00—20:00 የመጽሓፍ ቅዱሰ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳል:: እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ አንድ የጥናት ቡድን ይኖራል
  5. በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ18፡00 ሰዓት እስከ 20፡00 ሰዓት የምሽት ፀሎት ጊዜ አለን።
  6. ዘወትር እሁድ ከአራት ሰዓት (10፡00) እስከ አምስት ሰዓት ተኩል (11፡30) የታዳጊ ወጣቶች የአምልኮ ጊዜ በስዊድንኛ
  7. ዘውትር እሁድ ከአምስት ሰዓት (10፡30) እስከ ስድስት ሰዓት (11፡30) ድረስ የጸሎት ጊዜና
  8. ከአራት እሁድ ከስድስት ሰዓት (11፡30) እስከ ስምንት ሰዓት (13፡30) ድረስ የአምልኮ ጊዜ ይኖረና

  • ከ3 እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች የሰንበት ትምሕርት ይሰጣቸዋል
  • ከ13 እስከ 19 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን በየእሁዱ እናስተምራለን::
  • ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆናቸውን ስዊድንኛ ተናጋሪ ወጣቶች በአስራ አምስ ቀን አንዴ በዙም ረቡዕ ምሽት ፕሮግራም አላቸው

ክፍል ለማስያዝ ቤተክርስቲያን መሪዎች ይደውሉ:

የኢ. ወ. ቤ/ክ ሶሻል ሚድያ