የርህራሄና የእርዳታ አገልግሎት
“ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?” 1 ዮሐንስ 3፥17
የአገልግሎቱ ዓላማ
አገልግሎቱ የተጀመረው ከላይ በ1 ዮሐንስ 3፥17 ያለውን ክፍል መነሻ በማድረግ ሲሆን፤ ዋና ተግባሩም ክርስትያን ወንድሞችንና እህቶችን በሚያስፈልጋቸው ቁሳዊ ፍላጎቶች መርዳት ነው። የአገልግሎት ክፍሉም በዚህ ተግባር ውስጥ በረከት እንዳለ ያምናል።
የምናከናውናቸው ተግባራት
በአሁኑ ሰዓት አገልግሎቱ *** ቋሚ አባላት አሉት። እነዚህም አባላት በተለያየ ችግር ዉስጥ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ከተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ አካላት ጋር በመተባበር የተለያዩ ቸርነቶችን በየጊዜው ያደርጋሉ። ከእነዚህም መካከል፦
- ማረፊያ ቦታዎችን ማዘጋጀት
- የቤት ቁሳቁሶችን ማቅረብ
- የአልባሳት ስጦታን መስጠት
- የሥራ ዕድሎችን ማፈላለግ
- ወዘተ...
የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።
በተለያየ ምክንያት ችግር ከደረሰቦት ወይንም እርዳታ ከፈለጉ፤ ከታች የተጠቀሱትን የአገልግሎቱን አባላት በማናቸውም ሰዓት በአካል ወይንም በስልክ እንዲሁም በኢሜል ሊያነጋግሩ ይችላሉ።
አገልግሎቱን ለማገዝ
በስጦታዎ አገልግሎቱን ማገዝ ይፈልጋሉን? ማናቸውንም አይነት ቁሳዊ ወይንም የገንዘብ እርዳታ የአገልግሎቱ ክፍሉ በደስታ ይቀበላል። ይህንን ለማድረግ ልቦት ከተነሳሳ ፤ የአገልግሎቱን አባላት በማንኛውም ሰዓት ማነጋገር ይችላሉ።
የአገልግሎቱ አባላት
|
||
ሐብተስላሴ አበበ |
ውብዓለም አስፋው |
|
ስልክ ቁጥር: 000 00 000 00 |
||
ኢሜል: ###@###.### |