የመዘምራን አገልግሎት "ሀ"
"ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።" 1 ዜና 16፥9
አጭር ታሪክ
የመዘምራን ቡድኑ በመጀመሪያ በ1977 ዓ.ም. በስዊድን ስቶክሆልም አስር የሚሆኑ ሰዎች በማቀፍ ተመሰረተ። በጊዜው የመዘምራን ቡድኑ በሁለት ሳምንት አንዴ ጊዜ ብቻ በመገናኘት መዝሙር ያጠና ነበር። የአገልግሎት ቡድኑ ለቤተክርስቲያኒቱ በቋሚነት ከሚያቀርበው መዝሙር በተጨማሪ፤ በስዊድን ዉስጥ ለሚገኙ ሌሎች አጥቢያዎችና ከስዊድን ውጭ ባሉ ቤተክርስቲያኖች በመዘዋወር አገልግሏል።
የአገልግሎቱ ዓላማ
የ "ሀ"መዘምራን ቡድን ተቀዳሚ ዓላማ አማኞች በመደበኛ የአገልግሎት ጊዜያት እግዚአብሔርን በዜማና በመዝሙር እንዲያመልኩትና እንዲያወድሱት መምራት ነው። ይህንንም በማድረግ አማኞች በእምነት እንዲበረቱና እንዲፅናኑ ያደርጋል። በተጨማሪም ለቀጣዩ መደበኛ የቃል ጊዜ የተዘጋጀ ልብ በመፍጠር ያግዛል።
የልምምድ ጊዜ
የመዘምራን ቡድኑ በየሁለት ሳምንቱ ከ18:00 - 19:00 በቤተክርስቲያኒቱ መዝሙር ክፍል የመዝሙር ጥናት ያደርጋል። በልምምድ ጊዜ ከእኛ ጋር መዝሙር መስማትና ማጥናት ከፈለጉ፤ በተጠቀሰው ሰዓት ቦታው ላይ በመገኘት እግዚአብሔርን ማምለክ ይችላሉ።
የእሁድ አምልኮ
የመዘምራን ቡድኑ በየወሩ የመጀመሪያ እሁድ ከ11:00 - 11:30 መዝሙር ለጉባኤው ያቀርባል።
የአገልግሎት ቡድኑ አባላት
|
||
ብርሃነ ተወልደ |
ዳዊት ሰለሞን |
ኤልሳቤጥ ከበደ |
ኤፍሬም ቢተው |
ከበደ አለማየሁ |
ማክዳ ወልደገብርኤል |
መዓዛ ወንድምአገኝ |
ናትናኤል አበበ |
አሸናፊ ነጋሽ |