የኢየሩሳሌም ቤ/ክ የሽማግሌዎች አገልግሎት
ራዕያችን
የክርስቶስ ባህሪይ በቅዱሳን ህይወትና አገልግሎት ተገልጦ ማየት
ተልዕኮ
- የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መፅሐፍ ቅዱስን በማስተማርና በመስበክ ጤናማ የሆነ ደቀ መዝሙር ማፍራት
-
የታላቁ ተልእኮ ሃላፊነት ለመወጣት ምስክር የሚሆን ትውልድ ማስነሳትና ማሰማራት
-
አማኞች በአንድነትና በህብረት በመሆን ለመተናነፅና ለመደጋገፍ እንዲሁም በወንድሞች ሕብረት የታዘዘውን በረከት እንዲለቀቅ እና የበረከት ተካፋዮች ማድረግ
የቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ
- መፅሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተፃፈ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እናምናለን፣ እንዲሁም ሊታመንበት የሚገባ በሰው ልጅ እምነትና ህይወት ላይ የመጨረሻ ስልጣን ያለው የቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት እርሱ ብቻ መሆኑን እናምናለን
- ዘላለማዊ የማይወሰን ፍጹም የማይለወጥ ራሱን በሦስት አካል በአብ፤በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ የሚገልጽ በአንድ አምላክ ሁሉን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን
- ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ከድንግል ማርያም መወለዱን ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን፣ ስለ ሐጢያታችን በመስቀል የተሰቀለ፣የተሰቃየ፣የሞተ፣የተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ከሞት በአካል ተነስቶ ለሰዎች ተገልጦ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ መሆኑን አሁንም በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ዘውትር ስለ እኛ እንደሚማልድልን ዳግመኛም በታላቅ ክብር እና ስልጣን እንደ ሚመለስ እናምናለን
- በመንፈስ ቅዱስ አፅናኝ በአማኞች ውስጥ አድሮ መንፈሳዊ ስጦታዎችንና ሃይልን በማከፋፈል ቤተክርስቲያንን እንደሚቀድስና ዓለምን ስለ ኣጢያት፣ ስለ ፅድቅና ስለ ፍርድ እንደሚወቅስ እናምናለን፣እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በሃይል እንደሚያጠምቅና በልዩ ልዩ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እንደሚያስችል እናምናለን
- ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን በኣጢያት መውደቁንና በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን
- ደህንነትና የዘላለም ህይወት በክርስቶስ ኢየሱስ እንጂ በሌላ በማንም እንደማይገኝ እናምናለን
- በአማኝ የውሃ ጥምቀት እናምናለን
- ጌታችንና መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደሞተ የምናስታውስበትንና እንዲሁም ጌታ እስኪመጣ ሞቱንና ትንሳኤውን ለመናገር ከምዕመናን ጋር ያለውን ህብረት ለመግለፅ የጌታን እራት በመውሰድ እናምናለን
- ጌታችንና መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንግስቱን ለመመስረት ዳግም እንደሚመጣና ሙታንን እንደሚያስነሳና ለዘላለም በሚኖሩትና በሚሞቱት ላይ ፍርድን እንደሚሰጥና ሐጢያተኞች ከእግዚአብሔር ፊት ተለይተው በገሃነመ እሳት እንደሚቃጠሉ ፃድቃን ግን ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንደሚኖሩ እናምናለን
- በሙታን ትንሳኤ በሃጢያት ላይ በሚያደርሰው የዘላለም ፍርድና አማኞች በሚቀበሉት የዘላለም ሕይወት እናምናለን
የኢየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች
ዓላማ
የኢየሩሳሌም ወ. ቤ/ክ የሽማግሌዎች አገልግሎት ለቤተክርስቲያኑ መንፈሳዊም ሆነ አስተዳደራዊ ሂደት ሃላፊነት ያለው ነው::
ወንድም አሸናፊ ገብረሃና |
ወንድም ኤፍሬም ታከለ |
|
(0760741181) | (073-582 15 56) |