.
ዋናው ገጽ > የአገልግሎት ቡድኖች > የፀሎት አገልግሎት

የፀሎት አገልግሎት

"ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው..." የሉቃስ ወንጌል 18:1

የአገልግሎቱ ዓላማ

"ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።" ብሎ ዳዊት እደጸለየው የዚህ አግልግሎት መነሻ ዐላማ የእግዚአብሔርን ክብርና ሃይል እሁን በምንኖርበት ዘመን ተገጦ ለማየት ያለ ጉጉት ነው። ይህንንም ክብር ለማየት፣ እገልግሎቱ ሸክሙ ያላቸውን ቅዱሳን በማስተባባር ወደ እግዚአብሔር በጋራ በመጮህ ከእርሱ ዘንድ ታላቅ የሆነ ክብር እንዲገለጥ ጸሎትን በማስማማት ወደ እርሱ ያቀርባል።

ይህንንም እላማ ከግብ ለማድረስ የተለያዩ የቅብብሎሽ ጸሎቶችን በተለያየ ጊዜ እንዲደረጉ ክፍሉ ያስባብራል። የቅብብሎሽ ጸሎት መነሻ ሃሳብ ጌታ ኢየሱስ ሳናቋርጥ እንድንጸልይ በግል እና በቤተክርስቲያን ደረጃ ያዘዘንን ትእዛዝ መሰረት ያደረገ ነው። ጸሎት የክርስቲያንና የቤተክርስቲያን የህይወት ደም ስር እንደመሆኑ መጠን ከጤናማ ቤተክርስቲያን እና አማኝ ጀርባ ጤናማ የጸሎት ህይወት እንዳለም የሚያስረዳ ነው።

የቅብብሎሽ ጸሎት አገልግሎት አላማ ቅዱሳንን ለቤተክርስቲያን፣ ለኢትዮጵያ፣ ለኤርትራ፣ ለስዊድን፣ ለመሪዎች እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ባማከለ መልኩ ወደ ማያቋርጥ የጸሎት ህይወት እንዲግቡ ለማነሳሳት፣ ለማደራጀትና ለማበረታት ነው። ምንም እንኳን በቤተክርስቲያን ደረጃ በመሰባሰብ መጸለይ እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም የቅብብሎሽ ጸሎት አገልግሎት አላማ ግን ሁሉንም አማኞች በሚመቻቸው ጊዜ እና ቦታ በማስማማት ለጸሎት እራሳቸውን እንዲሰጡ ለማበረታታትም ጭምር ነው።

የምናከናውናቸው ተግባራት

ሁሉም የቤተክርስቲያን አባላትን በቅብብሎሽ ጸሎት እንዲሳተፉ ይበረታታሉ። ፈቃደኛ ሆነው በአግልግሎቱ ውስጥ የታቀፉት የሚመቻቸውን ሰዓት እና ቀን ባማከለ ሁኔታ በሳምንቱ ውስጥ ባሉት ቀናት በቡድን በመመደብ በተሰጣችው ቀን በየሳምንቱ መሪዎች በሚመርጡት ርእስ ላይ እንዲጸልዩ ይደረጋል። የጸሎት ርእሶቹን የአግልግሎቱ መሪዎች በየሳምንቱ የተለያየ ሚዲያዎችን በመጠቅም (በስልክ እና በኢሜል) ለአባላቱ ያስታውቃሉ። እንዲሁም እያንዳንዱ አባል ራው በሆነው ቀን ማስታወሻ እና የጸሎት ርእስ ነጥቦቹ በኤስኤምኤስ ይላክለታል። ይህን በየሳምንቱ በማድረግ የቅብብሎሽ ጸሎቱ እንዲቀጥል ይደረጋል።

በአመት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ የአገልግሎቱ አባላት አንድ ላይ በመሰባሰብ ትምህርት፣ ስልጠና እንዲሁም ማበረታቻ እንዲሰጣቸው ይደረጋል።

በአገልግሎቱ ለመሳተፍ

በቅብብሎሽ ጸሎቱ ውስጥ ለመካትት እና ቋሚ ተሳታፊ ለመሆን ከፈለጉ የአገልግሎት ዘርፍ አስትባባሪዎችን በማነጋገር በዚህ የጸሎት ሰንሰለት ውስጥ መግባት ይችላሉ።

አስተባባሪዎች

azebnigos01.jpg?nc=1460666308 mentwabwondimu01.0x100.jpg?nc=1459454075 samuelaga01.0x100.jpg?nc=1459454006
አዜብ ኒጎስ ምንትዋብ ወንድሙ ሳሙኤል አጋ

Tel: 000 00 000 00

Email: ###@###.###


ቋንቋ ምረጥ

ተጨማሪ ድረ ገጾች

ማስታወቂያዎች

መደበኛ (የዘወትር) ፕሮግራሞቻችን፤


  1. መጋቢዎቻችንን በሚከተለው ቁጥር ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ መጋቢ ንጉሱ ጉሌ (+46 (0)735115951) መጋቢ ወሰን ተሾመ (+46 (0)736162913)

  2. ሰኞ 10:00-14:00 የምክር አገልግሎት በወንድም ሙሴ ሃይሉ (በስልክ ቁ. 0707568264) በመደወል ልታገኙት ትችላላችሁ።
  3. ዘወትር ረቡዕ ከጥዋቱ አራት ሰዓት (10፡00) እስከ አስር ሰዓት (15፡00) የጾምና የጸሎት ጊዜ አለን
  4. ሀሙስ 18:00—20:00 የመጽሓፍ ቅዱሰ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳል:: እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ አንድ የጥናት ቡድን ይኖራል
  5. በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ18፡00 ሰዓት እስከ 20፡00 ሰዓት የምሽት ፀሎት ጊዜ አለን።
  6. ዘወትር እሁድ ከአራት ሰዓት (10፡00) እስከ አምስት ሰዓት ተኩል (11፡30) የታዳጊ ወጣቶች የአምልኮ ጊዜ በስዊድንኛ
  7. ዘውትር እሁድ ከአምስት ሰዓት (10፡30) እስከ ስድስት ሰዓት (11፡30) ድረስ የጸሎት ጊዜና
  8. ከአራት እሁድ ከስድስት ሰዓት (11፡30) እስከ ስምንት ሰዓት (13፡30) ድረስ የአምልኮ ጊዜ ይኖረና

  • ከ3 እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች የሰንበት ትምሕርት ይሰጣቸዋል
  • ከ13 እስከ 19 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን በየእሁዱ እናስተምራለን::
  • ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆናቸውን ስዊድንኛ ተናጋሪ ወጣቶች በአስራ አምስ ቀን አንዴ በዙም ረቡዕ ምሽት ፕሮግራም አላቸው

ክፍል ለማስያዝ ቤተክርስቲያን መሪዎች ይደውሉ:

የኢ. ወ. ቤ/ክ ሶሻል ሚድያ