የዲያቆናት አገልግሎት
"... እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።" ኤፌሶን 2፥10
የአገልግሎቱ ዓላማ
የዲያቆናት አገልግሎት ክፍል በዋነኝነት የሽማግሌዎች አገልግሎት ክፍል በቂ የሆነ የአገልግሎት ጊዜ ያግኝ ዘንድ የተለያዩ ተግባሮችን በሃላፊነት በመውስድ ይሠራል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስትያን ዲያቆናትን በሐዋርያት ሥራ 6፥ 2-4 ላይ አማኞችን በበጎ ሥራ ያገለግሉ ዘንድ እንደ ሾመች፤ ይህ የአገልግሎት ክፍልም የቤተክርስትያኒቱ ምእመናንን የተለያዩ በጎ ሥራዎችን በማድረግ ያገለግላል። ይህም በክርስቶስ እየሱስ የተሰጠንን መልካሙን ሥራ ለመሥራት ያግዛል።
የምናከናውናቸው ተግባራት
በአሁኑ ጊዜ የአገልግሎት ክፍሉ 5 ቋሚ አባላት ያሉት ሲሆን፤ እነዚህም በ1ጢሞቴዎስ 3፥ 8-10 ላይ እንደተቀመጠው መሥፈርት የተመረጡ ናቸው። በዚህ የአገልግሎት ክፍል አሁን እየተፈጸሙ ካሉ ዋና ተግባራት መካከል የሚከተሉት በዋነኝነት ይጠቅሳሉ።
- የቤተክርስቲያን ምእመኖችን በተለያዩ ጉዳዮች መርዳትና ማገዝ
- በቤተክርስቲያን አገልግሎት ጊዜ እንግዶችን መቀበልና ማስተናገድ
- በመደበኛ የአገልግሎት ጊዜ መባና አሥራት መሰብሰብ
- የቤተክርስቲያን ንብረት መቆጣጠርና አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ
- ወዘተ …
የአገልግሎቱ አባላት
|
|||
አልማዝ ዘራጽዮን |
ሃብተሥላሴ አበበ | ||
|
|||
ጳውሎስ ሰላም |
ሳባ ግርማ |
||
Tel: 000 00 000 00 |
|||
Email: ###@###.### |