እኛ ማን ነን?
አገር/ብሔር
የኢየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በስቶክሆልም ስዊድን የምትገኝ ኢትዮጵያውያንም ኤርትራውያንም አባላቶቻችን ያቀፈች አጥቢያ ስትሆን ከ200 መቶ ያላነሱ አባላቶች ያሉአት እ ኤ አ ከ1980 ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በስቶክሆልም ስትንቀሳቀስ የኖረች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት::
ስነመለኮታዊ አቋም
የእምነት አቋማችን ካሪዝማቲክ ፔንቴኮስታል ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን:: ስለእምነት አቋማችን በበለጠ ለማወቅ የእምነት መግለጫችንንና መሰረተ እምነታችንን እንዲሁም መተዳደሪያ ደንባችንን መመልከት ትችላላችሁ::
አመራር
ቤትክርስቲያናችን በመጋቢዎችና በሽማግሌዎች አገልግሎት ትመራለች::
ሳምንታዊ ፕሮግራሞች
- ሐሙስና እንደየአካባቢው በሌላ የሳምንት ቀን: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (17:30 - 19:30)
- በየሳምንቱ ቅዳሜ: የምሽት ፀሎት ጊዜ (18:00 - 20:00)
- ዘወትር እሁድ: ዋና የአምልኮ ጊዜ: 10:00 - 13:00
አመታዊ ኮንፍራንሶች
በዓመት ሶስት ጊዜ ኮንፍራንሶች ያሉን ሲሆን በገና በፋሲካና በክረምት (ሰመር) ጊዜ ለየት ያሉ ስብሰባዎችን (ኮንፍራንስ) አለን:: በተለይ በክረምት (በሰመር) ወቅት የሚኖረን ኮንፍራንስ በአጠቃላይ በኖርዲክ አገሮች (ዴንማርክ ኖርዌ ስዊድንና ፊንላንድ) ከሚገኙ አጥቢያዎች ጋር አብረን የምናደርገው ስብሰባ ነው:: በተጨማሪም ቤተክርስቲያናችን የአውሮፓ ሕብረት አባል እንደመሆኗ በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ እህት ቤተክርስቲያኖች ጋር የቤተክርስቲያን መሪዎች የተለያየ ልውውጥና ሕብረት አላት::