.
ዋናው ገጽ > የአገልግሎት ቡድኖች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አገልግሎት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አገልግሎት

"ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።" 1ጴጥሮስ 2፥3

የአገልግሎቱ ዓላማ

በራዕይ1፥3 ላይ እንደተፃፈው የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ፣ መስማትና ያዘዘውን ማድረግ ከክርስትና ዋና አስተምህሮቶች መካከል አንዱ ነው። በማቴዎስ 22፥29 ላይም ኢየሱስ ሰዱቃውያንን የእግዚአብሔርን ቃል ባለማወቃቸው ሲወቅሳቸው እናያለን። ስለዚህም ይህ የአገልግሎት ክፍል ምእመናን የጠለቀ የቃሉ ዕውቀትና መረዳት እንዲኖራችው ይሰራል። ይህንንም ተግባር በማድረግም በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰችው በሕብረት የጠነከረችና ታላቁን ተልእኮዋን የምትወጣ ቤተክርስትያን ያዘጋጃል።

የምናከናውናቸው ተግባራት

ጌታ እየሱስ አስራ ሁለት ሰዎችን መርጦ እንዳስተማረ፤ ይህ የአገልግሎት ክፍልም በጥቂት ሰዎች የተገነባ የቃል ጥናት ሕብረቶችን በተለያየ የከተማው ክፍል አዋቅሮ ይሰራል። በእነዚህም ሕብረቶች ውስጥ በቤተክርስትያን ያሉ ምእመኖች እንዲሳተፉ የአገልግሎት ክፍሉ በሚመቻችው ቅርበት ወዳለው የጥናት ሕብረት ቡድን ይመድባል። እነዚህም ትናንሽ ሕብረቶችን በማዋቀርና ምእመናን እንዲሳተፉ በማድረግ፤ የአገልግሎት ክፍሉ አማኞች የተሻለ ቅርርብና የቃል እውቀት መረዳት እንዲኖራችው ያግዛቸዋል ብሎ ያምናል።

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ፤ አገልግሎቱ ወርሃዊና ዓመታዊ የቃል ጥናት ዕቅዶችን ያዘጋጃል። በተማሪም ለሕብረቱ መሪዎች የሚሆን አስረጂ መፅሐፍቶችን እና በራሪ ወረቀቶችን ያዘጋጃል።

በአገልግሎቱ ለመሳተፍ

ሁሉም የኢየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አባሎች የቃል ጥናት ሕብረት ውስጥ መሳተፍ አለባቸው። በቃል ጥናቱ ውስጥ ካልታቀፉ፤ የቃል ጥናት ሕብረቶች የሚገናኙበትን ቀንና ሰዓት በመመልከት ወይንም የሕብረቱን አስተባባሪዎች በማናገር ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ። የተለያየ ጥያቄ ካሎትም የአገልግሎቱ ክፍሉን በማናችውም ሰዓት ማነጋገር ይችላሉ።

የአገልግሎቱ አስተባባሪዎች

adisuketema01_107x0.0x100.jpg?nc=1461695

tadelechwanna01_92x0.0x100.jpg?nc=146169

ጳውሎስ

ታደለች ዋና

ስልክ : 000 00 000 00

ኢሜል :

ንዑሳን ድረገጾች


መልእክት ሊያስተላልፉልን ከወደዱ ይሄንን ይጫኑ...

ቋንቋ ምረጥ

ተጨማሪ ድረ ገጾች

ማስታወቂያዎች

መደበኛ (የዘወትር) ፕሮግራሞቻችን፤


  1. መጋቢዎቻችንን በሚከተለው ቁጥር ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ መጋቢ ንጉሱ ጉሌ (+46 (0)735115951) መጋቢ ወሰን ተሾመ (+46 (0)736162913)

  2. ሰኞ 10:00-14:00 የምክር አገልግሎት በወንድም ሙሴ ሃይሉ (በስልክ ቁ. 0707568264) በመደወል ልታገኙት ትችላላችሁ።
  3. ዘወትር ረቡዕ ከጥዋቱ አራት ሰዓት (10፡00) እስከ አስር ሰዓት (15፡00) የጾምና የጸሎት ጊዜ አለን
  4. ሀሙስ 18:00—20:00 የመጽሓፍ ቅዱሰ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳል:: እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ አንድ የጥናት ቡድን ይኖራል
  5. በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ18፡00 ሰዓት እስከ 20፡00 ሰዓት የምሽት ፀሎት ጊዜ አለን።
  6. ዘውትር እሁድ ሶስት ሰዓት (09፡00) እስከ አራት ሰዓት (10፡00) ድረስ የጸሎት ጊዜና
  7. ከአራት እሁድ ከአራት ሰዓት (10፡00) እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል (12፡30) ድረስ የአምልኮ ጊዜ ይኖረና

  • ከ3 እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች የሰንበት ትምሕርት ይሰጣቸዋል
  • ከ13 እስከ 18 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን በየእሁዱ እናስተምራለን::
  • ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆናቸውን ስዊድንኛ ተናጋሪ ወጣቶች በአስራ አምስ ቀን አንዴ እሁድ ከሰዓት በኋላ (ሙሉ ቁጥር ሳምንታት) በቤተክርስቲያን ፕሮግራም አላቸው

የኢ. ወ. ቤ/ክ ሶሻል ሚድያ