የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት
የአገልግሎቱ ራእይ
- ሌሎችን ለክርስቶስ ለመማረክ ስንጣጣር የእኛኑ ልጆች በእግዚአብሔር መንግስት እንዳናጣቸው!
- ለክርስቶስ የተማረከ ትውልድን ማፍራት!
- ቤተክርሰቲያንን የሚረከብ ትውልድን ማፍራት!
- በእኛ ትውልድ ዘንድ ያለው የእግዚአብሔርን እሳት ለሚከተለው ትውልድ ማስተላለፍ!
- ከእኛ ይልቅ የጨከኑ የእግዚአብሔር ሰዎች እንዲወጣቸው!
የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት ዓላማ
- የደህንነት ውሳኔ ያላደረጉ እንዲወስኑ መርዳት
- የወሰኑት በእግዚአብሔር ቃል ተኮትኩተው እንዲያድጉና እንዲጠነክሩ መርዳት
- በትምህርት ቤትና በሕብረተሰብ ታዳጊ ወጣቶች የሚገነባባቸውን ምሽግ በእግዚአብሔር ቃል ማፍረስ
- የክፋትን አሰራር ማጋለጥ ማፍረስና መመከት
- ለቤተሰብና ለቤተክርስቲያን የበኩላችንን እገዛ ማድረግ
- መልካም ሕብረት በመካከላቸው እንዲፈጠር ማድረግ
- በትምሕርት በኑሮ ውሳኔዎች በሕይወት ጥያቄዎች ለታዳጊ ወጣቶች ድጋፍ መሆን
- በአምልኮና በሌላውም መድረክ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ማበርከት
- እግዚአብሔር ለእያንዳንዳቸው ያለውን ዓላማ እንዲያውቁ መርዳትና ማነሳሳት
- እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸውና ለውጥ የሚያመጡ እንዲሆኑ መርዳት
የታዳጊ ወጣቶች የመሰብሰቢያ ጊዜአት
- ዘወትር እሁድ 10፡00 እስከ 11፡30 ሰዓት (በፈረንጆች ሰአት አቆጣጠር) የአምልኮና የትምህርት ጊዜ
- በሳምንት አንዴ ወይንም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ በትንንሽ ቡድኖች በወጣቶች መሪዎች ይሰበሰባሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናሉ፣ ቁምነገር አዘል ጭውውቶችን ያደርጋሉ
- የጽሞና ጊዜ/ሪትሪት - በዓመት ሁለት ወይንም ሶስት ጊዜ - ወጣ ያለ ቦታ ይዘናቸው በመሄድ ለሁለት እስከ ሶስት ቀናት የተለያዩ ጠለቅ ያሉ ትምሕርቶችን በመስጠት፣ የሕብረት ጊዜ እንዲያሳልፉ በማድረግ መሪዎች (፱ናችንና አንዳንድ ወላጆች ሆነን) አብረናቸው ጊዜ እናሳልፋለን።
- የተለያዩ የትምሕርትና የጸሎት ወዘተ ስብሰባዎች ለወጣቶቹ አልፎ አልፎ ይኖረናል።
የአገልግሎት ቡድኑ አባላት

የአገልግሎት ቡድኑ የሚሰበሰብበት መደበኛ ጊዜ፤
- በየሳምንቱ ራቡዕ ምሽት የፀሎትና እቅድ የማውጫ ጊዜ
- በወር አንድ ጊዜ የጸሎትና የማቀጃ ጊዜ
- በተጨማሪም እንደየአስፈላጊነቱ የአካልና የዙም ስብሰባ ያደርጋል
ንዑሳን ድረገጾች
- በተለያዩ ርእሶች ላይ የተዘጋጁ ትምሕርቶች (በስዊድንኛ)
- የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራሞች (በቪዲዮ)
- የታዳጊ ወጣቶችና የስዊድንኛ ተናጋሪ ወጣቶች አገልግሎት ሪፖርት ለአባላት



