2017-12-01 "...እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም..."
22 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦23 ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦24 እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤
25 እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤
26 እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።
27 እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ። (ዘኍ. 6:22-27)


