የወጣቶች አገልግሎት
ራዕይ (Shared vision)
ከተቀበልነው ጸጋ የተነሳ እግዚአብሔርን እያመለክን በክርስቶስ ፍቅር እርስ በርሳችን ተያይዘን የምስራቹን ወንጌል ለሰውልጆች ሁሉ በማዳረስ ህብረተሰባችንን በአካል ፣ በአእምሮና በመንፈስ የእግዚአብሔርን ሀሳብ ማስታጠቅና ለታላቁ
ተልዕኮ ማሰማራት።
ተልዕኮ (Mission)
1. በእውነትና በመንፈስ እግዚአብሔርን ማምለክ እንችል ዘንድ እውነት የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር።ይህም አምልኮ በወጣቱ በዕለት ከዕለት ሕይወት ወስጥ ተግባራዊ እንዲሆን መትጋት
2. በሕብረቱ የተረሳ እስከማይኖር ድረስ ወጣቶች እርስ በርሳቸው በክርስቶስ ፍቅር እንዲያያዙ ፣ እንዲዋደዱና
እንዲተሳሰቡ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
3. የምስራቹን ወንጌል ለወጣቶች በተለያዩና ዘለቄታ ባላቸው መንገዶች መድረስ።
4. የእግዚአብሔር ብርቱ ክንድ በወጣቱ ሕይወት እንዲሁም በወገኖቻችን ሁሉ ይንቀሳቀስ ዘንድ ህብረቱ (ወጣቱ)
አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር እንዲፀልይ ማበረታታት
5. ወጣቶች እንደመንፈሳዊ ዕድገታቸው በሚያስፈልጋቸው በማንኛውም ነገር በክርስቶስ ምሳሌ ሙሉ ሰውነት
እንዲደርሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
6. በወጣቱ የሚመሩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና ለጋሽ መንፈሳዊና መንፈሳዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን
በማፈላለግ የተቸገሩትን ወገኖቻችንን መርዳት
7. ወጣቱ በሚያነሳቸውና ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የምክር አገልግሎት መስጠት
8. ለወጣቱ ወቅታዊ የሆኑ ለመንፈስና ለስነ-ልቦና ዕድገት ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችን በማዘጋጀት እንዲሁም የታወቁ
አስተማሪዎችን /ጠቀሜታ ያላቸው ትምህርቶችን/ በመጋበዝ ወጣቱ ዕውቀት እንዲኖረውና በጉዳዮቹም ላይ
እንዲወያይ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
መርሆች (Core Values)
1. የመጨረሻ ስልጣን ባለቤት ለሆነው ለእግዚአብሔር ቃል እንገዛለን። ዮሐ 1-12. እግዚአብሔር በክርስቶስ ፍቅር እንዳሰበን በማወቅ በፍቅር ሕይወት እንመላለሳለን። 2ኛ ዮሐ 1-5
3. በግልም ሆነ በወጣቱ ህብረት ለሰራነው ሥራ በእግዚአብሔር እንዲሁም በአጠገባችን ላሉት ወጣቶች ተጠያቂዎች
ነን። እንደብርሃን ልጆች ሥራችን ሁሉ በግልፅነት የተሞላ እንዲሆን እንጥራለን ።ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፥9-10
4. ለሥራ ያለን አክብሮት በቤተ-ክርስቲያንም ሆነ በግል ኑሮአችን ያላሰለሰ እንዲሆን እንጥራለን።
5. የተቀበልነውን ራእይ ለመወጣት/ተልዕኮአችንን ለመፈፀም ከስሜትና ሌሎች ከማያንፁ ድርጊቶች በመጠበቅ
የመንፈስ አንድነት እንዲኖረን እንተጋለን። ዘዳ 19፥9-10
6. በእግዚአብሔር በተሰጠን የቤተ-ክርስቲያኒቷ መሪዎችና ቤተ-ክርስቲያኒቷ በምትመራው መተዳደሪያ ደንብ
እንገዛለን።
7. በህብረት ለማደግ እንተጋለን።
8. በህብረቱ ያሉ ወጣቶች በሙሉ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እንተጋለን። 2ኛ ጢሞ 1-6
9. የወጣቱ ማንነትና ሃሳብ በመካከላችን መከበር ስላለበት ለዚህ እንጥራለን።
መሪዎች
አሸናፊ ገብረሃና |
ዳዊት ማቴዎስ |
ሉድ ተሾመ | በፈቃዱ ዋለልኝ |
መሳይ አለሙ |
ሊያገኙን @JEC Youth Fellowship/Ungdoms Gemenskap
ፎሎው ቤተ ክርስቲያን @JECSweden
ሞባይል +46700244884 (ሉድ ተሾመ)